ARBEGNOCH/ETHIOPIAN PATRIOTS
  • Home
  • About Us
    • Album
    • Board Members
    • Formation
  • Donate
  • Stories
  • News
  • Contact
  • Print Sale
  • Merchandise Sale
  • Home
  • About Us
    • Album
    • Board Members
    • Formation
  • Donate
  • Stories
  • News
  • Contact
  • Print Sale
  • Merchandise Sale

About us

EN | AM
Archeologists have confirmed by the discovery of remains in the rift valley including DINKINESH (LUCY) and ARDY that Ethiopia is the cradle of mankind. Lucy had lived in Ethiopia 2.5 million years ago.

Nine hundred years before the birth of Christ, Ethiopia accepted Judaism ; over 2000 years ago began to practice the Christian faith; and on the 4th century A.D. she accepted Muslim immigrants who left their country for fear of persecution. The three religions have lived side by side peacefully up to the present day.
​

 It is proven beyond any doubt that Ethiopia is a country that does not like to annex territories of other nations and does not allow any country to infringe into her territory. History testifies to this account. Ethiopia is said to be blessed by God with rivers, lakes, wild animals and fertile grounds. Over the years, this has tempted countries close and afar to colonize and subjugate its people.  Ethiopians residing in Northern Shoa created the Association of Ethiopian Patriots in 1939. This organization was instrumental in coordinating the struggle against the invading Italian Fascist Force. It is now an organization with the following mission:
  • Chronicle historical conditions, perspectives, battles and sacrifice of the Arbegna.
  • Maintain records of all registered Arbegna – living and deceased.
  • Educate the younger generation of the Arbegna unwavering determination to maintain the independence of Ethiopia.
  • Raise funds to augment the financial aid provided to the Arbegna by the Ethiopian Government.
  • Associate with like-minded organizations and humanitarian agencies.

የኢትዮጵያ ታሪክ በአጭሩ፤
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዐርበኞች ታሪክ በአጭሩ ለመዘከር ከኢጣሊያ ወረራ በፊት የነበረውን የኢትዮጵያን ታሪክ በአጭሩ መዳሰስ ለአንባቢው መጠነኛ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ እና መንደርደሪያም እንደሚሆን ስለታመነበት እነሆ ቀርቧል::
​
ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ዘር መገኛ መሆኗን የሥነ ስብእ ተመራማሪዎች (አንትሮፖሎጂስቶች) ከድንቅነሽ(ሉሲ)
በአርዲ ቅሪተ አካል በመነሣት አረጋግጠዋል:: ድንቅነሽ በኢትዮጵያ ምድር ከዛሬ ሁለት ሚሊዮን ተኩል ዓመት (2.5 ሚሊዮን) በፊት በኢትዮጵያ ምድር ላይ የኖረች ኢትዮጵያዊት መሆኗ ተረጋግጧል::

ኢትዮጵያ ዘጠኝ መቶ ዓመት(900) ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ላይ የኦሪትን ሕገ አምልኮ፤የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት (2000) ክርስትናን ተቀብላለች፡፡ በ4ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሃይማኖት ምክንያት ተሰድደው በመጡ ጊዜ ክርስቲኑ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ተቀብሎ በሠላም እንዲኖሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡ ከዚያን ጊዜ አንሥቶም እነሆ ሦስቱ እምነቶች ተቻችለው ለመኖራቸው በታሪክ ያስመሰከረች ግምባር ቀደም አገር ለመሆኗ ተረጋግጦላታል:: ስለሆነም የማንንም አገር የማትመኝ  ከማንኛውም አገር ጋር በሠላም ለመኖር የምትሻ አገር መሆኗ ከረጅም ዘመን የታሪክ ማህደሯ ለማወቅ ይቻላል::

አገራችን በተፈጥሮ የታደለች ለልማት ሊውሉ የሚችሉ በርካት ወንዞችና ሐይቆች ያሏት፤ በከርሰ ምድሯ የተለያዩ ማዕድናት የያዘች፤ የመሬቷ ልምልሜ ማራኪ፤ ያሉዋትም የዱር አራዊትና አእዋፋት በየትም ዓለም የማይገኙና ብርቅዬ ለመሆናቸው የተረጋገጠ፤ በመሆኑና የጂኦግራፊ አቀማመጧ ወሳኝ በመሆኑ፤ የመስፋፋት ዓላማ የነበራቸው የቅርብና የሩቅ አገር ወራሪዎች ሁሉ ጉልበታቸው መፈርጠሙን ሲያምኑ በመዳፋቸው ሥር አድርገው ሊጠቀሙባት ሕዝቧንም ጨቁኖ ለመግዛት ከመመኘትና ምኞታቸውንም ተግባራዊ ለማድረግ ከመሞከር ተቆጥበው አያውቁም::
  • ሮማዊያን በ29 ዓመት ከክርስቶሰ ልደት በፊትና በ48 ዓመተ ምሕረት፤
  • ከ16ኛው ምዕተ ዓመት ጀምሮ የቱርክ፤ የፖርቱጋል፤ የግብጽ፤ የሱዳን መሀዲስቶች፤ የእንግሊዝና የኢጣሊያ ወራሪዎችን በመመከት ነጻነቷን አስከብራ ኖራለች ::​
​
 አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት በርሊን ላይ እ.አ.አ.በ1884/1885 ባደረጉት ስብሰባ ኢጣሊያ ድርሻዋን ለመውሰድ በ1888 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ወረረች::

በዳግማዊ ዐፄ ምኒልክና በእቴጌ ጣይቱ ብጡል አመራር ሰጪነትና ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል በዘመተው በጀግናው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፤ በወቅቱ ዘመናዊ መሣሪያ ታጥቆ የመጣው የኢጣሊያ ጦር አድዋ ላይ ተሸንፎ የሐፍረት ማቅ ተከናንቦ እንዲወጣ አድርገውታል:

ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ስለመውረሩዋ፤ 
ፋሽስቶች ኢጣሊያንን ከተቆጣጠሩ በኋላ፤ በ1888 ዓ.ም. በኢጣሊያ ላይ በአንድ የጥቁር ሕዝብ አገር የደረሰባቸውን ውርደት ለመበቀል፤ በአገራቸው የተከሰተውን የኤኮኖሚ ቀውስ ለማስተንፈስ፤ በኢትዮጵያ ለም መሬት ተጠቅሞ መጠነ ሰፊ ምርት ለማካበት፤ ሥራ ፈቱን የሰው ሀይላቸውን ለመታደግ ሲባል ለኋላ ቀሯ ኢትዮጵያ "ሥልጣኔን ለማጎናጸፍ ተነሣስተናል"በሚል የቅኝ ገዢዎችን የተለመደ የቅጥፈት ምክንያት አንግበው ኢትዮጵያን ለመውረር ሙሶሊኒ፤ ሮም ላይ መስከረም 21 ቀን 1928 ዓ. ም. በአደረገው ንግግር “.....የዓለም መንግሥታት ማኀበርን ለ13 ዓመት፤ ኢትዮጵያን ለ40 ዓመት ታገሥን፤ አሁን ግን በቃ.......” ብሎ በመፎከር በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት አወጀ::                                        

ኢጣሊያን 40 ዓመት ሙሉ  በዘመናዊ መሣሪያ ትጥቋን ስታዘጋጅ ቆይታ ኢትዮጵያ ደግሞ ጦርነቱ ከመጀመሩ ከ3 ዓመት በፊት ጀምሮ፤እራሱዋን ለመከላከል ስትል ዘመኑ ያለፈባቸውን መሣሪያዎች ከዚህም ከዚያ በመግዛት ጦሩዋን ለማዘጋጀት በምትንቀሳቀስበት ወቅት መስከረም 22 ቀን 1928 ዓ.ም.የኢጣሊያን ጦር መረብን ተሻግሮ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ገባ :: 
ኢትዮያውያን በተንቤን፤በአምባራዶም፤በሽሬ፤በቆራሄ፤በገናሌ፤በኦጋዴንና በማይጨው እስከ መጋቢት 30 ቀን 1928 ዓ.ም. በአደረጉት ታላልቅ ጦርነቶች የአገራቸውን ሉዐላዊነት ለመጠበቅ ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ሕይወታቸውን ሰውተዋል፡፡ ሆኖም የጠላት ኀይል አመዝኖ የኢትዮጵያ ጦሮች ለማፈግፈግና ጦርነቱን በአርበኝነት ለመቀጠል ተገደዋል::
የኢትዮጵያ ጦር ለማፈግፈግ የተገደደው ጀግንነትና ቁርጠኝነት አንሶት ሳይሆን ከብዙ ምክንያቶቹ መካከል ጥቂቶቹ፤
  • ውጊያዎቹ ሁሉ የተካሄዱት ጊዜ ባለፈባቸው መሣሪያዎች ሲሆን ጣሊያኖች አርባ(40) ዓመት ሙሉ ለጦርነት በመዘጋጀትና የዳበረ የኤኮኖሚ አቅም በማደራጀታቸው በመሆኑ 
  • የዘመናዊ የጦር ትምህርት ያላቸው የሠራዊት ቁጥር እጅግ አናሳ በመሆኑ፤
  • የጠላት ኃይል የአውሮፕላን ኃይል በመጠቀሙ እና 
  • ጠላት በዓለም የተከለከለውን የጋዝ መርዝና ጢስ  በመጠቀሙ እንደሆነ ታምኖበታል:: 

የጠላት ጦር እየገፋ ሲመጣ የመንግስት አመራር የሚሰጥበት ወደ ጎሬ፤ኢሉባቦር በተባለ በደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ሚገኘው እንዲዛወርና ትግሉ በአርበኝነት እንዲቀጥል ተወስኖ  ንጉሠ ነገሥቱም በሊግ ኦፍ ኔሽን ስብሰባ ላይ ተገኝተው ለዓለም መንግስታት አቤቱታ ለማቅረብ ወደ ጄኔቫ እንዲያመሩ በመወሰኑ ይኸው ተግባራዊ ሆኑዋል::  

​ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጠላት ድል ሆኖ ከአገር እስከተባረረበት ቀን ድርስ ዐርበኞች በመላ ኢትዮጵያ በቡድን በቡድን ተደራጅተው በየጎበዝ አለቃቸው መሪነት ጠላትን እንቅልፍ አሳጥተው እንደባነነ፤አንቀላፊኝ በተባለ በሰሜን ሸዋ በምትገኝ ሥፈራ ጥቂት አርበኞች አንቀላፊኝ በተባለ ሥፍራ ተሰባስበው ጥር 1 ቀን 1931 ዓ.ም. የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጃግኖች አርበኞችን ማህበር በማቁዋቁዋም ትግሉ በትብብር ተቀናጅቶ ጠላት በአምስት ዓመት ቆይታው እፎይ ሳይል፤ አስተማማኝ የኑሮ ዋስትና ሳያገኝ፤ ውርደቱን ተከናንቦ ከመደምሰስ የተረፈው የጠላት ጦር ወደመጣበት መመለሱን ይፋ ያደረገው ሚያዝያ 27 ቀን1933 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በአዲሰ አበባ በክብር ተሰቅሎ እንዲውለበለብ በተደረገበት ወቅት ነበር፡፡

​ዐርበኝነትና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዐርበኞች ማኀበር ምሥረታ:-
የኢትዮጵያ ዐርበኞች በየአከካባቢዎቻቸው የሚያደርጉትን ውግያ ማስተባበሩ የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው በመገንዘብ፤ በአንድ ድርጅት ጥላ ሥር ለመሰባሰብና ትግሉን ለማፋፋም በሰሜን ሸዋ ተጉለት ውስጥ በሚገኘው አንቀላፈኝ በተባለ ሥፍራ በክቡር ራስ አበበ አረጋይ ሊቀ መንበርነት ዐሥር ዐርበኞች ስብሰባ አካሂደው ጥር 1 ቀን 1931 ዓ. ም.”የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ማኀበር--ኅብረ ሰማዕታት መዋዕያን” በሚል ስያሜ ማቋቋም ችለዋል :: ይህም ማኀበር በየክፍለ ሀገሩ ያሉትን የዐርበኞች ቡድኖች አስተባብሮ ትግሉን በመቀጠል ሚያዝያ 27 ቀን 1933  ዓ. ም. ላይ ድልን በመቀዳጀት ጠላት ተሸንፎና አፍሮ ወደመጣበት፤ የውርደት ማቁን ተከናንቦ እንዲመለስ አድርገዋል::  

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዐርበኞች ማኀበር አባሎች ሚያዝያ 13 ቀን 1954 ዓ. ም. እንደገና አዲስ አበባ ውስጥ በሰባ(70)  ዐርበኞች ተወክለው ታላቅ ስብሰባ ተካሂዶ የማኅበሩን የመጀመሪያ የመተዳደሪያ ደንብ አጽድቀዋል:: 

ከሐምሌ 18 ቀን 1959 ዓ.ም. ጀምሮ ማኀበሩ ከመንግሥት ሕጋዊ ዕውቅና አግኝቶ እነሆ፤ ዓላማውን እውን ለማድረግ በተለያዩ ወቅቶች የመተዳደሪያ ደንቡን እያሻሻለ እስከዛሬ ድረስ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል:: 

​የማኀበሩ ዓላማዎች በአጭሩ፤
  • ለአንድነትና ለነጻነት የተደረገውን ተጋድሎ ለተተኪዉ ትውልድ ማሳወቅ፤
  • ጀግኖች አባትና አናት ዐርበኞች ያደረጉትን ተጋድሎ በታሪክ ማኀደር በመዘክርነት ማስቀመጥ፤
  • ለተረካቢው ትውልድ አኩሪ የጀግንነት ታሪክ እንዲረከቡ ማመቻቸት፤
  • ለተጋደሉትና አሁን በዕርጅና ዘመን ላይ ያሉትን ዐርበኞች የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ  የሚደጎሙበትን መንገድ መቀየስ፤
  • ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር እርዳታ ማሰባሰብ፤
  • ከግል ለጋሾችና ከዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች የሚገኙ ዕርዳታዎችን በልማት ሥራ ላይ ማዋል፤
  • በውጭ አገር ካሉ አቻ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመመሥረት​ መረዳዳትን መፍጠር ናቸው፡፡


Support an Arbegna

The Association aims to provide the basics – food, water, medicine, preventive care, and shelter – for the aging patriots and their families. We urge anyone that is willing and able to chip-in and make a donation. They deserve our gratitude.